የተፈጥሮ ማዳበሪያ ማምረቻ እና ማሰልጠኛ ማዕከል

በሸገር ከተማ በገላን ጉዳ ክ/ከተማ፤ ሰበታ አከባቢ በባዮና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ፤ ከሰበታ ከተማ አስተዳድር እና ከኦሮሚያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ባለስልጣን ጋር በመተባበር እየተከናዋነ ያለው የኮምፖስት ማምረቻ እና ማሰልጠኛ ማዕክል ስራ። ዋና ዓላማ የከተማ ደረቅ ቆሻሻና ኢንዱስትሪ ፍሳሽ በተቀነጀ ሁኔታ ወደ ተፈጥሮ ማደበሪያ መቀየርና ለከተማ ግብርና ማዋልና የአካባቢ ብክለትን መከላከል ነው። በማዕክሉ በዋናነት የዊንድሮው ኮሚፖስቲንግ እና የቨርሚ-ኮሚፖስቲንግ ቴክኖሎጂዎች በመጠቀም የከተማ ደረቅ ቆሻሻን ወደ ተፈጥሮ ማዳበሪያ የመቀየር ስራ የተሰራ ሲሆን ፤ በተጨማሪ የዊንድሮው ኮሚፖስቲንግ ስራን ለማቅለል የኮሚፖስት ማገላበጫ (Compost turner) በተቋም ዲዛይን ተደርጎ ጥቅም ላይ አንዲውል ተደርጎል:: በቀጣይ የስራውን ደረጃ ከፍ በማድረግ በብዛት በማምርት በማሽን ፈጭቶ፤ በመንፋትና አሽጎ ከአጠቃቀም መመሪያ ጋር ለተጠቀሚ ለማደረስና ለበርካታ ወጣቶች የስራ እድል ለመፍጠር በስፋት እየተሰራ ይገኛል፡፡ ይህን መሰል ስራዎች በየከተማው ቢሰሩ እና ከከተማ ግብርና ጋር ቢቀናጁ ትርጉም ባለው መንገድ የማህብረሰቡን ህይዎት ሊቀይሩ የሚችሉና ተግዳሮትን ወይም ብክለትን ወደ መልካም እድል መቀየር የሚያስችሉና በሀገር አቀፍ ደረጃ በከተማ ግብርና ለተጀመረው ስራ ውጤታማነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚኖረው ይሆናል።

Leave a Reply